Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እግርኞችና ብስክሌተኞች በተለያዩ ከተሞች ፊስቲቫል አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሽከርካሪ ነጻ የእግርኞችና የብስክሌኞች ጉዞ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተለያዩ ከተሞች ተካሄዷል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከጷግሜ እስከ ጷግሜ እንደርሳለን በሚል መሪ ሃሳብ በወር አንዴ በሚያከናውነው በዚህ መርሃ-ግብር የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተከናውነዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው ፕሮግራም ላይ ስፖርተኞች እና የከተማዋ ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፥ ሞተር አልባ የትራንስፖርት ስትራቴጂን መጠቀም የትራፊክ አደጋን ከመቀንስ አኳያ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የአዕምሮ ጤንነትን ከማሻሻል፣ የአየር ብክለትን ከመቀነስ እንዲሁም የፓርኪንግ አገልግሎት ችግርን ለማቃለል ያለው ሚናም ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ሚኒስትሯ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ጥራት ያለው ሞተር አልባ ትራንስፖርትን ለመፍጠር የከተማ መንገዶችን ለእግረኞች እና ለብስክሌተኞች ምቹ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።
በተመሳሳይ የአማራ ክልል ከተሽከርካሪ ነፃ የእግርና የብስክሌት ጉዞ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፌስቲቫል በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ውቤ አጥናፉ፤ በክልሉ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በአማካይ በቀን የ3ሰው ህይወት ያልፋል ብለዋል።
ይህን ችግር ለመፍታት የስልጠናና የቁጥጥር ስርዓቱን የተሻለ በማድረግ ቢሮው እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ክላል ሳህለማርያም አስከፊውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን ባለደረባችን ሳምራዊት የስጋት ዘግባለች፡፡
በአሰላ ከተማ በተካሄደው ስነ-ስርዓት ላይ የተለያዮ ስፖርታዊ ክንዋኔወች፣ 5 ኪ.ሜ የሸፈነ የብስክሌት እና 200 ሜ የሸፈነ የፖራ ኦሎምፒክ እንዲሁም የ3 ኪ.ሜ የእግር ጉዞ እና የፈረስ ጉግስ ተካሂዷል።
በ2012 አ.ም በጅማ ከተማ መንገዱ የሰዉ ነው እንደርሳለን በሚል መሪ ቃል የተጀረዉ ስነስረአቱ በኦሮሚያ ክልል ለ 11 ኛ ጊዜ ከቋግሜ እስከ ቋግሜ እንደርሳለ” በሚል መሪ ቃል በአሰላ ከተማ ተካሂዷል።
በኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬክተር እና የትራፊክ አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ዋቅጅራ የትራፊክ ፍሰትን ለመቀስ ጤናማ እና ሰላማዊ የእግር ጉዞዎች እናዘውትር ስሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሊያ ዱጉማ እና ጀማል ገንዶ ዘግበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version