Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቁጫ የምርጫ ክልል ድምጽ ቆጠራ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት የቁጫ የምርጫ ክልል ድምጽ ቆጠራው እየተካሄደ ነው ያለው።
የቁጫ የምርጫ ቁጥር ማዳመር ተጀምሮ የነበር ሲሆን አለመግባባቶች በመፈጠራቸው ተቆጠራው አንድ አንድ እጩ በተገኘበት ቆጠራው በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው።
ሒደቶች በጥሩ ሁኔታ ከተከናወኑ በኋላ ነው ቆጠራ ላይ አለመግባባቶቹ የተከሠቱት።
ከእያንዳንዱ ፓርቲ የተወከሉ ሰዎች በተገኙበት በአሁኑ ሰዓት ቆጠራ እየተደረገ ነው።
86 ጣቢያዎች በምርጫ ክልሉ ያሉ ሲሆን በአስራ አንዱ (11) ላይ አቤቱታ እንደቀረበባቸው ነው የተገለጸው፡፡
በሌላ በኩል 11 የምርጫ ጣቢያዎች ታዛቢወች ተደብድበዋል።
ከቆጠራው በፊት በነበረ የምርጫ ቦርድ እና የተወካዮቹ ውይይት ላይ ተነስቷል።
86 የክልልና 86 የተወካዮች ም/ቤት ታሽገው የመጡ የድምጽ ሳጥኖች እየተቆጠሩ ነው፡፡
በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version