አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡
በሃዘን መግለጫቸው የሚሊየኖች እናት፣የእናትነት ፣ የደግነት፣ የፍቅር፣ የቆርጥነት እና የጥንካሬ ምሳሌ”ኢትዮጲያዊቷ ማዘር ትሬዛ” እያልን በበጎ ምግባራቸው የምናከብራቸዉ፤ የምንሳሳላቸዉ፤ ረጅም ዕድሜና ጤና ስንመኝላቸዉ የኖርን ተምሳሌታችን ዶክተር አበበች ጎበና (እዳዬ) በማረፋቸዉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።
ከእኛ በአካል ቢለዩም የጀግንነትና የመልካምነት ስራቸው ከመቃብር በላይ በመሆኑ ሁሌም ሲወደሱ ፣ ሲታወሱ፣ ሲመሰገኑና በልባችን ህያው ሆነው ይኖራሉ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ፡፡
ለልጆቻቸው ፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉና ለመላዉ የከተማዋ ሕዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡
የጀመሩት መልካም ስራ ለአፍታ እንደማይቋረጥም ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

