Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በወረባቦ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በ3 ሺህ 400 ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወረባቦ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በ3400 ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ሙአዝ መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ የአንበጣ መንጋው ከሰኔ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአከባቢው ተከስቷል፡፡
መንጋው 10 በመቶ የሠብል ምርት ለይ እና 5 በመቶ በግጦሽና በቁጥቋጦዎች ላይ ጉደት ማድረሱን ተናግረዋል።
የአንበጣ መንጋውን ለመከላከልም ማህበረሰቡ በባህላዊ መንገድ ጥረት እያደረገ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ሀላፊው በዘመናዊ መንገድ ለመከላከል የአውሮኘላን እርጭት ለማድረግ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version