Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የክልሉ ምክር ቤት 2 ቢሊየን 292 ሚሊየን 810 ሺህ 681 ብር የ2013 ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት 2 ቢሊየን 292 ሚሊዮን 810 ሺ 681 ብር የ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት አፀደቀ።
ይህ በጀት በክልሉ የገቢ አሰባሰብ መጨመሩንና የሀብትና መሰረተ ልማት ፍላጎት መጨመሩን መሠረት አድርጎ ነው ተብሏል።
ከጀቱ ውስጥ 477 ሚሊየኑ ለተጓተተቱ ፕሮጀክቶች የሚውል ሲሆን÷1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ለደመወዝና ለሌሎችም ወጪዎች ይውላል ነው የተባለው።
62 ሚሊየኑ ደግሞ ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ይዉላል የተባለ ሲሆን አዋጁም 187/2013 ሆኖ ፀድቋል።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version