Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች መሰጠት መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለፈተናው 10 ሺህ 319 ወንድ እና 7 ሺህ 639 ሴት ተማሪዎች በድምሩ 17 ሺህ 958 የቀንና የማታ ተማሪዎች እንደተቀመጡ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት እንዳሉት ÷ክልል አቀፍ ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በ186 የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን 523 ፈታኞች ይገኛሉ፡፡

የፈተናው ደህንነት እንዲጠበቅ በሁሉም አካባቢዎች የፈተና ወረቀት ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆይ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ፈተናው በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version