አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት የወጣቶች አረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት በተለያዩ ክልሎች መካሄዱ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ማስጀመርያ ክልላዊ ፕሮግራም በአዊ ዞን በባንጃ ወረዳ በገምባሃ ቀበሌ በደመቀ ሁኔታ አካሂደዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመርያ ፕሮግራሙ በአዊ ዞን በባንጃ ወረዳ በገምበሃ ቀበሌ በርካታ ችግኞችን በመትከል የተጀመረ ሲሆን ÷ማህበረሰቡ በአከባቢዉ ችግኞችን በመትከል የመሬትን ዘላቂነት እንዲያረጋግጥ እና እንዲንከባከብ እዉቀት እና ግንዛቤ እንዲኖረዉ አስችሏል ተብሏል።
በፕሮግራሙ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት ጋሻዉ ተቀባ ተገኝተዉ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በክልል ደረጃ 4ነጥብ 5 ሚልየን ወጣቶች የሚሳተፉበት 800 ሚልየን ችግኝ ለመትከል አቅደዉ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚህ ፕሮግራም ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተወከሉ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ አመራሮችና አባላት፣ ከፍተኛ የዞን እና የክልል አመራሮች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ የተወከሉ ወጣቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች መገኘታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
51
Engagements
Boost Post
49
2 Shares
Like
Comment
Share