አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከአለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ኤዲ ሮው ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ አምባሳደር ይበልጣል ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብና የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው÷ በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር ተቀራርበው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን በሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

