አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና አስከሬን ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ መስቀል አደባባይ ሽኝት እየተደረገለት ነው፡፡
የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና የአስከሬን ስንብት መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው አስታውቋል።
የቀብር ስነ ስርዓታቸውም በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ9 ሰዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
ስርዓተ-ቀብራቸው ከመከናወኑ በፊት ከረፋድ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5 ሰዓት በመኖሪያ ቤታቸው የአስክሬን ሽኝት መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በመረሃ ግብሩ መሰረት ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በመስቀል አደባባይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በሚገኙበት አሸኛኘት እንደሚደረግ ከአበበች ጎበና የህጻናት ክብካቤና ልማት ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።

