Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሚዛን አማን አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሚዛን አማን ከተማ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው በይፋ ተጀመረ።

በ925 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባው አየር ማረፊያ በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ነው የተገለፀው።

አየር ማረፊያው ከአራት አመታት በፊት ይገነባል ተብሎ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲነሳ የተደረገ ቢሆንም ከአራት አመታት በላይ ሳይጀመር በመቅረቱ የህዝብ ቅሬታ ፈጥሮ መቆየቱን የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን ከበደ ገልፀዋል።

ሰኔ አስር ቀን 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግንባታው በይፋ ሊጀመር ችሏል።

የአየር መንገዱ ተቋራጭ ሳምሶን ቸርነት ጠቅላላ ተቋራጭ ባለቤት አቶ ሳምሶን ቸርነት ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ በማጠናቀቅ ለማስረከብ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በአደም አሊ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version