አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤ ኤን – 26 የተባለው የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን መሰወሩ ተሰማ፡፡
የአካባቢው ባለስልጣናት አውሮፕላኑ 28 ተጓዦችን ይዞ ሲበር እንደነበረና በመሀል ከአውሮፕላኑ አብራሪ ጋር የሚደረግ ግንኙነት እንደተቋረጠ አስታውቀዋል፡፡
አውሮፕላኑ በሩቅ ምስራቅ የሩሲያ ክፍል በካምቻትካ የውሃ ዳርቻ አካባቢ ሳይሰወር እንዳልቀረም እየተነገረ ነው፡፡
የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለግ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል ፡፡
አውሮፕላኑ ከፔትሮፓቭሎቭስክ – ካምቻትስኪ ተነስቶ መዳረሻውን ፓላና የውሃ ዳርቻ በማድረግ ሲበር እንደነበረ ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

