አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት እየተገነባ ባለው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች እንዲሁም ማህበረሰቡ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
በትምህርት ቤቱ ጊቢ ውስጥ ዛሬ የተጀመረው ችግኝ ተከላ በ3 ቀናት ውስጥ 12ሺህ ችግኞችን በአካባቢውም ጭምር ለመትከል እቅድ መያዙን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ባስገነባቸው ትምህርት ቤቶች ሁሉ ችግኞችን በተማሪዎቹ ማስተከል እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን፥ ፅህፈት ቤቱ በችግኝ ተከላው የተሳተፉትን አመስግኗል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

