Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

77 ሺህ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በደሴ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱንም የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አበበ ገብረ መስቀል የአቅመ ዳካሞችን ቤት በማደስ አስጀምረዋል።
የደሴ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ፈንታዬ ጋሻው፥ በዚህ ክረምት ወቅት 18 የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ ተዘጋጅተናል ነው ያሉት።
የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አባይነህ መላኩ እንዳሉት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ጀምሮ በግብርናው፣ በጤናውና በሌሎች ዘርፎችም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ምንጭ ፡- አሚኮ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version