Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሃገር-አቀፍ የትምህርት ቤቶች ምገባ ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ  ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገር-አቀፍ የትምህርት ቤቶች ምገባ ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ  ይፋ ሆኗል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አገር አቀፍ የትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ማጽደቂያ ስነስርአት ላይ ÷ ለጸደቀው የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲና ስትራቴጂ ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር የተማሪዎችን ለረሃብ ተጋላጭነት በማስቀረት የተሟላ ጤናና ስርአተ ምግብ እንዲሁም የተሻለ የትምህርት አቀባበልና ውጤት እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አስረድተዋል።

መርሃ-ግብሩ የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ከማሻሻል ጎን ለጎንም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው አስረድተዋል።

ዛሬ የጸደቀው የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲና ስትራቴጂ የ ሰነድ ዋና አላማም  ለሁሉም የቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቆይታቸው በየእለቱ በንጥረ ምግብ የበለጸገ ምግብ ለማቅረብ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

በዚህም የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት በማሻሻል ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ማገዝ መሆኑን  ዶክተር  ጌታሁን መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version