አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገሌ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምርጫ ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው።
የነገሌ ምርጫ ክልል ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ አማኑኤል ብርሃኑ ከ150 በላይ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች መመደባቸውን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት በተጀመረው የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመከላከል ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በነገሌ ምርጫ ክልል ለሁለቱም ምክር ቤቶች ሁለት በግል፣ አንድ ከኢዜማ እንዲሁም አራት ከብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች ለውድድር መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው ምርጫ አንድ የግል እጩ ተወዳዳሪ ባቀረቡት ቅሬታ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንዲቋረጥ መደረጉን የነገሌ ምርጫ ክልል ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ አማኑኤል ብርሃኑ አስታውሰዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

