አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የግብጽና የሱዳን ህዝቦች የአባይ መነሻ ኢትዮጵያ መሆኑን ተርድተው አብሮ መጠቀም እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ገለጹ።
በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ግቢ ችግኝ በመትከል በሀገሪቱ ባሉ መስጂዶች ችግኝ የሚተከሉበትን መርሃ ግብር አስጀምረዋል።
የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ጨምሮ የመስጂድ ኢማሞችና የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች በተገኙበት በጽህፈት ቤቱ ግቢ በጋራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ተካሂዷል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ኢትዮጵያ የህዝቦችን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ በምትገነባው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የግብጽና የሱዳን ወገኖች የሚያደርጉት ጫና ከእምነት አስተምሮ ያፈነገጠ በመሆኑ ሊያስቡበት ይገባል።
አብሮ በመስራት እንጂ በእኩይ ተግባር ማደግ አይቻልምም ነው ያሉት ።
በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ መስጂዶችና በተለያዩ የእምነቱ ተቋማት ቦታዎች ችግኝ እንዲተከል ሲሉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ጥሪማቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

