Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጃኮብ ዙማ እጃቸውን ለፖሊስ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤት በመዳፈር ወንጀል የተላለፈባቸውን የ15 ወራት እስራት ለመፈፀም እጃቸውን ሰጡ፡፡

ፕሬዝዳንቱ የተላለፈባቸው የእስር ቅጣት በመኖሪያ አካባቢያቸው ኩዋዙሉ ናታል ኢስት ኮርት ማረሚያ ቤት እንደሚፈፀምም ነው የተገለጸው ፡፡

የ79 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት የእስር ቅጣቱ የተላለፈባቸው በሙስና ክስ ላይ መረጃ እንዲሰጡ ተጠይቀው ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ክስም ሆነ የእስራት ቅጣት በቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንቶች ላይ ተፈፅሞ እንደማያውቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የጃኮብ ዙማ ፋውንዴሽን በመግለጫው የቀድሞው ፕሬዝዳንት በመጀመሪያ እጃቸውን ለህግ አካል ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም ኋላ ላይ ግን መስማማታቸውን ነው ያስታወቀው፡፡

የጃኮብ ዙማ ልጅ ዱዱ ዙማ በትዊተር ገጿ አባቷ እንደታሰረና በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስታውቃለች፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version