Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች 2 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርጓል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፅህቤት ሃላፊ አቶ ክበበው ወርቅነህ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደገለፁት÷ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ የሀገሪቱ ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ለተረጂ ወገኖች የሚቀርቡ ድጋፎች በአግባቡ መሰራጨታቸውን ከክልል ተቋማት ጋር በመተባበር ክትትል እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ በበኩላቸው÷ በተለያዩ መንገዶች የሚቀርቡ ድጋፎችን ለተረጂዎች ለማድረስ በየደረጃው ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ለዜጎች ዘላቂ ጠቀሜታን በሚሰጡ ድጋፎች ዙሪያ አተኩረን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እንዲሁም የገቢዎች መምሪያ ሃላፊና የዞኑ የግብዓት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ባንቲሁን መኮንን÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው እንደ ተቋማቱ ሁሉ አቅም ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶችም ለተፈናቀሉ ለዜጎች እርዳታ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የተደረጉ ድጋፎች ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የህፃናት ጫማና አልባሳት፣ ማካሮኒ፣ ፓስታ፣ ብስኩትና መመገቢያ ቁሳቁስ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
በሙሉጌታ ደሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version