Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፀጥታው ምክር ቤት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተፋሰሱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት እንዲወያዩ ድጋፍ ማድረጉ ተገቢ ነው- ዶክተር አረጋዊ በርሔ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታው ምክር ቤት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተፋሰሱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት እንዲወያዩ ድጋፍ ማድረጉ ተገቢ መሆኑን ዶክተር አረጋዊ በርሔ ተናገሩ፡፡
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀስ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ዶክተር አረጋዊ በርሔ እንደተናገሩት÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለግድቡ ግንባታ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን 16 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰብ ተችሏል።
የዲያስፖራው ማህበረሰብ ለግድቡ ግንባታ እያደረገ ያለው ተሳትፎ መጨመሩንም ገልፀው÷ በ2013 ዓ.ም ብቻም ዲያስፖራው ለግድቡ ግንባታ 1 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማዋጣቱንም ለአብነት ጠቅሰዋል።
የፀጥታው ምክር ቤት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተፋሰሱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት እንዲወያዩ ድጋፍ ማድረጉ ተገቢ መሆኑንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version