Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ5 ወራት ውስጥ 67 ከተሞችን የ4ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌ ኮም በአምስት ወራት ውስጥ 67 ከተሞችን የ4ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ኢትዮ ቴሌ ኮም በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ፈጣን የአራተኛው ትውልድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ በጎንደር ከተማ በይፋ አስጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግበሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የተቋሙ ደንበኞች ተገኝተዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ÷ ተቋሙ ዲጅታል ኢኮኖሚን በሀገሪቱ ለመገንባት ስትራቴጂ ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የደብረታቦር እና የጎንደር ከተማ ደንበኞችም የ4ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መጠቀም የሚችሉ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በአራተኛው ትውልድ 103 ከተሞችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ÷ ባለፉት 5 ወራት 67 ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ በሌሎች ከተሞችም የ4ጂ ኢንተርኔት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ጥረቱን እንደሚቀጥል ነው የገለጹት።
በሁለት ወራት ውስጥ በቴሌ ብር 6 ሚሊየን ተጠቃሚዎች መፍጠር መቻሉንም ወይዘሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል፡፡
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version