Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በወላይታ ዞን የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ ÷ መርሃ ግብሩን የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ ችግኝ በመትከል እና ደም በመለገስ አስጀምረዋል፡፡
አስተዳዳሪው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰባችንን በተግባር የምናገለግልበት መሆን እንዳለበት ነው የገለጹት፡፡
የዞኑ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ፀጋ ፋንታ በበኩላቸው÷ በወላይታ ዞን ከ250 ሺህ በላይ ወጣቶች በመርሃ ግብሩ ላይ እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
በጥላሁን ሁሴን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version