አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በምርጫው የተወዳደሩ ግለሰቦች ልምዳቸውን እያካፈሉ ነው።
የግል እጩው አቶ አለሳ መንገሻ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ትምህርት የተወሰደበትና የቦርዱን ገለልተኛነት ለማረጋገጥ የተሰራበት ነው ብለዋል።
ምርጫው አሳታፊ መሆኑ የቦርዱ አባላት ምርጫ በሂደቱ የተሻለና ትምህርት የቀሰምንበት ነው ብለዋል።
የተሻለ ስራ ለመስራት ግን አሁንም ቀሪ የቤት ስራ አለብን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በጫናዎች ውስጥ ሆና የተሻለ ስራ ሰርተናል፣ አሁንም ፈተናዎችን ለመሻገር በጋራ መቆም ይገባናልም ነው ያሉት።
የብልፅግና እጩ ሆነው የተወዳደሩት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በሀሰተኞች ሸንጎ ባሸነፈችበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በፈተና ውስጥ ሆና በምርጫውና በህዳሴው ግድብ ታሪክ ሰርታለች ነው ያሉት።
ምርጫ ቦርድ በሴቶች ተመርቶ ውጤታማ መሆኑ እድል ከተሰጣቸው የማይችሉት እንደሌለ ያሳያልም ነው ያሉት።
በዚህ ምርጫም የሴቶች ተሳትፎ የተሻለ የሴቶች የመቻል መንገድ መጀመሩን ያሳየ ነውም ብለዋል።
ምርጫው የኢትዮጵያ አሸናፊነት የታየበት ትልቅ በታሪክ እጥፋት መሆኑንም ኢንጅነር አይሻ ተናግረዋል።
የፖለቲካ ፓርቲ እጩዋ ፀጋነሽ ጋማቶ በበኩላቸው÷ ምርጫው ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የገለጠችበት ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ማጭበርበርና መቶ በመቶ አሸንፈናል የሚባልበት እንደነበር አንስተው÷ አሁን ግን ነፃ ተቋም በማቋቋም የተካሄደ ነው ብለዋል።
የግል እጩው ብሩክ ቢያድግልኝ በበኩላቸው ባለፉት አመታት በአፍ ብቻ የዲሞክራሲ ስርአት እንደነበር ገልፀው÷ ነፃ ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ መቋቋሙን አንስተዋል።
ቦርዱም የተለያዩ ስራዎችን መስራቱንም ነው የጠቆሙት።
ምርጫው ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል ባይልም ህዝቡ የድምፁን ዋጋ የተረዳበት፣ ወደፊት ለሚሰሩ ስራዎችም ተስፋ የሰጠ ነው ብለዋል።
ሆኖም የተለያዩ ችግሮች ገጥሞታል ሲሉም አክለዋል።
የግል ተወዳዳሪው አቶ ገላሳ ዲልቦ አስቀድመው በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ኢትዮጵያ ስላገኘችው ዲፕሎማሲያዊ ድል እንኳን ደስ አለን ብለዋል።
ምርጫውና የግድቡ ሂደት ለኢትዮጵያዊያን ተስፋ የሰጠ ብለውታል።
ምርጫውም ከስርቆትና ውዝግብ ተላቆ በአዲስ ምዕራፍ የተካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ምርጫው ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሥርአት መሰረት የጣለ እንደሆነም አክለዋል።
በአፈወርቅ እያዩ

0
People Reached
135
Engagements
Boost Post
127
3 Comments
5 Shares
Like
Comment
Share

