አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 385 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሀፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 572 ሴቶችና 112 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 385 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

