አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የሚመሰረተው ፓርላማ ውጤታማ እንዲሆን የሚያግዘው ጽህፈት ቤት ሊኖር ይገባል ተባለ።
በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎና ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለን ጨምሮ የምክር ቤቱ እና የጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡
በመድረኩ ላይ አሁን ያለውን የጽህፈት ቤት አደረጃጀት በመከለስ አማራጭ የአደረጃጀት ጥናት በባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን÷ጥናቱ የህንድ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የቦትስዋና እና የእንግሊዝ ፓርላማ ጽህፈት ቤቶች ተሞክሮን የዳሰሰ ስለመሆኑ የጥናቱ አቅራቢዎች ገልጸዋል፡፡
እንደ ጥናቱ አቅራቢዎች ለሀገራችን ካለው አስፈላጊነት እንዲሁም አቅምን ባገናዘበ መልኩ የየሀገራቱን ልምድ በመቀመር የተዘጋጀው ይህ አደረጃጀት ምክር ቤቱን በማዘመን ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ያስችለዋል ተብሏል፡፡
የቀረበው የአደረጃጀት ጥናት የምር ቤቱን ስራዎች በጥልቀት የዳሰሰ መሆኑና አሁን በስራ ላይ ያለውን የጽህፈት ቤት አደረጃጀት ክፍተቶች ለማቃናት እንደሚያግዝ በቀረበው ጥናት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ከፍተኛ አመራሮች ጠቁመው፤ ጥናቱ ሊፈትሻቸው ይገባል ያሉትን ምክረ-ሃሳብም ሰንዝረዋል፡፡
የአደረጃጀት መዋቅሩ ብቻውን ውጤታማ እንደማያደርግና የሰው ኃይል አስተዳደሩና ፍትሃዊ የድልድል መመሪያ ማዘጋጀት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ መገለጹን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

