Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 6 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ ሃገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በዚህ መሰረት በትናንትናው ዕለት 633 ሴቶችንና 248 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 6 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version