አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም 7 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሚኒስትሮች፣ የክልሉ ፣ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአሶሳ ወረዳ ሐምሌ 02 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።
“ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ሃሳብ በሚከናወነው 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 72 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙን ቢሮው ገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ ክረምት የሚተከሉ ችግኞች 28 ሺህ 881 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት እንደሚሸፍኑም ነው የተገለጸው፡፡
በክልሉ የፊታችን ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ብቻ 7 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ቢሮው አስታውቋል፡፡
ለዚህም የክልሉን ደን ለማሻሻል የሚያስችሉና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ህብረተሰቡም በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝቶ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

