አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡
መርሃ ግብሩ “በወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል ነው የተጀመረው፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና ወጣቶች ተገኝተዋል፡፡
የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በሀዋሳ ከተማ ታቦር ተራራ የተከናወነ ሲሆን ÷ የወጣቶች የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ደግሞ በሀዋሳ ከተማ በሶስት ክ/ከተሞች የአቅመ ደካሞችን ቤት ጥገና እና እድሳት በማድረግ ተጀምሯል፡፡
አቶ ደስታ ሌዳሞ የዘንድሮው የበጎ ተግባራት እንቅስቃሴ ካለፋት ዓመታት ለየት የሚያደርገው ወጣቱ በነቂስ በመውጣት በምርጫው ለብልፅግና ፓርቲ ያለውን ድጋፍ ባሳየበት ወቅት መሆኑ አንስተዋል፡፡
እንደ ሲዳማ ክልል ለዘንድሮው “ኢትዮጵያን እናልብሳት መርሃ ግብር” 300 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙን ነው አቶ ደስታ የተናገሩት፡፡
ወጣቶች ዛሬ የተከሉት ችግኝ እንዲሁም የሚሰሩት በጎ ስራ ነገ ለሀገር ተረካቢው ትውልድ የሚመች አካባቢ እና ሀገር መፍጠር እንደሚያስችል መግለጻቸውንም ከሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

