Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር 392 ሚሊየን ችግኞች ተተከሉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም በአንድ ጀምበር 350 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ 392 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በዘንድሮው ዓመት 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል በሀገር አቀፍ ደረጃ መታቀዱ የተገለፀ ሲሆን ÷በዘንድሮው መርሃ ግብር የሚተከሉት ችግኞች ለደን፣ ለመኖ እና ለምግብነት የሚውሉ እንዲሁም ለብዙአገልግሎት የሚውለው ቀርቀሃ መሆናቸው ታውቋል።
ፎቶ-ኦ ቢ ኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version