አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከሱዳን ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የተመለከተ ውይይት ተደረገ
በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር እና የውጭ ዜጎች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አምባሳደር ኦሳማ ማጁብ ሐሰን ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ከሱዳን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ዜጎች የሚገጥሟቸውን አንዳንድ ችግሮች ለመቅረፍ በጋራ ለመስራት ተወያይተዋል።
በዚህ ረገድ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ መረጃ መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ፣ ለወደፊትም በቅንጅት በመስራት ችግሩን አስቀድሞ ለመከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ለመምከር እና የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ዜጎች ሲያጋጥሙ ደግሞ በቶሎ ወደ ሀገራቸው ስለሚመለሱበት መንገድ መክረዋል።
ከዚሁ ባሻገርም የኢትዮጵያን እና የሱዳንን ታሪካዊ እና ወንድማማቻዊ ግንኙነት በማውሳት ከድንበሩ ጋር በተያያዘ ያሉ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባም ሃሳብ መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

