Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ በጋራ የ100 ቤቶችን አድሳት አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ በአዲስ አበባ የ100 አቅመ ደካሞችን ቤቶች አድሳት አስጀምረዋል።

መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተቋማቱ ላደረጉት ተነሳሽነትና በጎ ተግባር አመስግነዋል።

በለውጡ ሂደት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተለመደና ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው ይሄው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሄራዊ ሎተሪ ለቤቶቹ እድሳት በጋራ ያዋጡትን 10 ሚሊየን ብር ምክትል ከንቲባዋ ተረክበዋል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌውን ጨምሮ የተቋማቱና የአስተዳደሩ ሰራተኞች እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዘንደሮው ክረምት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2 ሺህ አቅመ ደካሞችንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች መኖሪያ ቤቶች ለማደስ ታቅዷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version