አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 553 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 106 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ 125 ሰዎች በቫይረሱ በጽኑ መታመማቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰአታት 65 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ÷ ሁለት ዜጎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

