አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ዘርፎች ውጤት መመዝገቡን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በበጀት ዓመቱ የንድፈ ሀሳብ ፈተና ከወሰዱት 134 ሺህ 857 ሰዎች መካከል 91 ሺህ 775 ማለፍ የቻሉ ሲሆን ÷የማለፍ ምጣኔን 75 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 68 በመቶ ማሳለፍ ተችሏል፡፡
ይህ የማለፍ ምጣኔ ከ2012ዓ.ም በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ ብልጫ አለው ነው የተባለው፡፡
በተያያዘም የተግባር ፈተና ከወሰዱት 110 ሺህ 809 ሰዎች መካከል 79 ሺህ 967 ወይም የዕቅዱን 72 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
በአዲስ ተሸከርካሪዎች ምዝገባ፣ በተሸከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ፣ የአሽከርካሪዎች አሰልጣኝ ግለሰቦች እና ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና ተያያዥ ሥራዎችም ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

