አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪፐብሊካን የጥበቃ ሀይል በአራዳ ክፍለ ከተማ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደ አዲስ ያደሳቸውን ስድስት የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት ለተጠቃሚዎች ዛሬ አስረክቧል።
ቤቶቹ ከዚህ ቀደም ጣሪያቸው የሚያፈስ፣ ንፋስ የሚያስገቡ የጭቃ ቤቶች ሲሆኑ፤ የሪፐብሊካን የጥበቃ ሀይል አባላት ከደመወዛቸው በማዋጣት ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ቤቶቹን በብሎኬት አስገንብተው አስረክበዋል።
ከቤቱ እድሳት በተጨማሪም የአልጋ፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ እና አንሶላ ስጦታ በሪፐብሊካን የጥበቃ ሀይል አባላት የቤት እድሳት ለተደረገላቸው ሰዎች ተሰጥቷል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሀና የሺንጉስ ክፍለከተማው በክረምት ወራት 190 ቤቶችን ለማደስ እንዳቀደ ገልጸዋል።
የሪፐብሊካን የጥበቃ ሀይል የቤት እድሳት ስራውን ግንባር ቀደም በመሆን በጥራትና በፍጥነት ቤቶቹን አድሶ ለነዋሪዎች ማስረከቡን ተናግረዋል።
ክፍለ ከተማው በክረምት ወራት ሊያድስ እቅድ ከያዛቸው 190 ቤቶች በተጨማሪ በጎ ፍቃደኞችን በማሳተፍ አዳዲስ 80 ቤቶችን አካቶ የእድሳት ስራ እየሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

