አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ህፃናት ወደ ጦርነት መግባት የለባቸውም እንደ እኛ የመማር ዕድል ሊያገኙ እንደሚገባ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
በመስከረም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቷን የምትከታተለው ተማሪ አዳነች ኃይሉ ከሰሞኑ በማህበራዊና በታዋቂ የውጭ ሚዲያዎች ሳይቀር በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ መከታተሏን ትናገራለች፥ በተለይ ህጻናት ወደ ጦርነት እየገቡ መሆኑ አሳስቧታል፡፡
‹‹እነዚህ ህፃናት እኛ ያገኘነውን የትምህርት ዕድል ማግኘት ሲገባቸው በጦርነት እንዲሳተፉ ማድረግ አይገባም›› በማለት ስሜቷን ገልጻለች፡፡
‹‹ህጻናት እንደኛ መማር አለባቸው ስለሆነም ዓለም አቀፍ የህፃናት መብት ድርጅቶች ይህንን ጉዳይ ሊያወግዙና ሊያስቆሙ ይገባል›› ስትልም ትጠይቃለች፡፡
በተመሳሳይ በትምህርት ቤቱ የ3ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ በሱፍቃድም የተማሪ አዳነችን ሀሳብ ይጋራል፡፡
በትግራይ ክልል ያሉ ህጻናት እንደሌሎች የሀገሪቱ ህፃናት ጊዜያቸውን በትምህርት ቤት ማሳለፍ ሲገባቸው ወደ ጦርነት እንዲገቡ መደረጉ ተገቢ አይደለም ይላል፡፡
ሰሞኑን ከትግራይ ክልል የሚወጡት የፎቶግራፍ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ህጻናት ያለእድሜያቸው የጦር መሳሪያ ተሸክመው በጦርነቱ እንዲሳተፉ ተደርገዋል፡፡
ይህ ድርጊት የህጻናትን ደህንነት ለመጠበቅ ከወጣው ዓለም አቀፍ ህግጋት አንጻር ሲታይ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ቢሆንም፤ ለህጻናት ተቆርቋሪ የሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድርጊቱን ሲያወግዙት አይታይም ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

