አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) አዲስ ስታንዳርድ ኦንላይን ሚዲያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣውን አዋጅ በመተላለፉ መታገዱን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን አስታውቋል።
ጊዜያዊ ዕገዳው የተላለፈበት በባለስልጣኑ የክትትል ግኝቶች ፣ ቅሬታዎች እና ከሽብርተኛው ህወሓት ቡድን ጋር ያለውን ግንኙነት ተከትሎ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ኦንላይን ሚዲያው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን በመተላለፍ እንዲሁም የህወሓት ሽብር ቡድንን አጀንዳ ማስፈጸም ላይ ሲሰራ መቆየቱም ተመላክቷል፡፡
በእነዚህ እና ሌሎች ተዛማጅ የሥነ ምግባር ጉድለቶች ጥልቅ ምርመራ የሚደረግባቸው ሲሆን÷ ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰድበት እንደሚችልም ባለስልጣኑ ጠቁሟል፡፡
ለፕሬስ ነፃነት ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ እናረጋግጣለን ያለው ባለስልጣኑ ÷ ሁሉም ሚዲያ ተቋማት የጋዜጠኝነት ሙያ ስነ ምግባርን መሰረት በማድረግ እና የህግ የበላይነትን በማክበር በኃላፊነት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

