Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወደ ትግራይ ለሚገባ ሰብአዊ ድጋፍ አስፈላጊውን ፍተሻ ለማድረግ የሚያስችሉ ተጨማሪ የፍተሻ ማሽኖች እየተተከሉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ትግራይ ክልል የሚገባ ማንኛውም ሰብአዊ ድጋፍ ተገቢው ፍተሻ ተደርጎለት በአፋጣኝ ለተረጅዎች እንዲደርስ ለማስቻል ተጨማሪ የፍተሻ ማሽኖች እየተተከሉ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በሰጡት መግለጫ ምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን የያዙ 61 ከባድ ተሽከርካሪዎች መቐለ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ሌሎች ተመሳሳይ ቁሳቁሶችን የጫኑ 60 ከባድ ተሽከርካሪዎችም በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ በመግባት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ወደ ትግራይ የሚገባ ማንኛውም ሰብአዊ ድጋፍ ተገቢው ፍተሻ ተደርጎለት በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን ተጨማሪ የፍተሻ ማሽኖች ተከላ በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

በሰርዶና አፍዴራ ሁለት የፍተሻ ማሽኖች እየተገጣጠሙ መሆኑን ጠቅሰው የ10 ማሽኖች ግዥ እንደሚከናወን መናገራቸውን ተናግረዋል፡፡
በመንግስት በኩል የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ የተወሰነበት ዋነኛ ምክንያት አርሶ አደሩ ክረምቱ ሳያልፍ እንዲያርስ መሆኑን አስታውሰው በዚህም 12 ተሽከርካሪዎች 10 ሺህ 350 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ጭነው የፍተሻ ጣቢያ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
በመታገስ አየልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version