Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የህጻናት ሳይንስ ማዕከል አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የህጻናት ሳይንስ ማዕከል አስመረቀ፡፡
የሳይንስ አካዳሚው በኢትዮጵያ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኤኖቬሽን ዘርፍ ጥናትን መሰረት ያደረጉ ምክሮችን በመስጠትና ምርምሮች የማድረግ ስራ እየሰራ ይገኛል።
ተቋሙ በኢትዮጵያ ሳይንስን ለማሳደግ ከመሰረቱ ጀምሮ መስራት ስለሚገባ ይህ የህጻናት ሳይንስ ማዕከል እንደተቋቋመ የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ፕሮፈሰር ጽጌ ገብረማርያም ገልጸዋል።
የሴቶችና ህጻናት ወጣቶች ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የተጠናከረ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲኖር ህጻናትና ወጣቶች ላይ የሚሰራው ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው በዚህ ረገድ ሳይንስ ማዕከሉ የሚኖረው ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።
የህጻናት ሳይንስ ማዕከሉ በጎተ ኢንስቲቲዩት ኢትዮጵያ እና በፋኖሜንታ ድጋፍ የተሰራ ነው።
በዘመን በየነ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version