አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሰው የጋምቤላ ክልል ልዩ ሃይል አባላት ዛሬ ማምሻውን የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክን ጨምሮ የክልሉ አፈ-ጉባኤ አቶ ጁል ናንጋልናጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት አቶ ኡሞድ የክልሉ ልዩ ሃይል ወቅቱ ለሚፈልገው ሀገራዊ ተልዕኮ ከሀገር መከላከያ ሰራት ጎን በመቆም ግዳጁን ይወጣል ያሉ ሲሆን ÷የክልሉ መንግስትም ኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን የውስጥና የውጭ ትንኮሳ ለማክሸፍ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣ አስታውቀዋል፡፡
የልዩ ሃይል አባላቱ በበኩላቸው ÷የሀገርን አንድነት ለማፍረስና የህዝቡን የተረጋጋ ህይወት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

