አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አምነስቲ ኢንተርናሽናል ‘የትግራይ ተወላጆች እየታሰሩ ነው’ በሚል ለፈጠረው የሃሰት ክስ የተጠቀመው ፎቶ የምርጫ ዕለት ከመራጮች ሰልፍ ላይ የተወሰደ መሆኑ ተጋለጠ።
ፎቶ ግራፉን ያነሳው ግለሰብ አማኑኤል ስለሺ የሚባል ሲሆን፥ በትዊተር ገጹ ላይ ይፋ እንዳደረገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግስትን ለመወንጀል የተጠቀመው ፎቶ ግራፍ ከአውዱ ውጪ ትርጉም እንዲይዝ ተደርጎ ጥቅም ላይ መዋሉን አጋልጧል።
የምርጫውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ያለውን ሁኔታ ለማሳየት ለኤኤፍፒ የላከው ፎቶ መሆኑን ገልፆ፥ ‘‘የትግራይ ተወላጆች እየታሰሩ ነው’’ ለሚል ውንጀላ መዋሉ ስህተት መሆኑን አመልክቷል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናልም ፎቶውን ከገጹ ላይ እንዲያወርደው መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

