Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጀርመን እና እንግሊዝ የስራ ጉብኝት አድር

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጀርመን እና እንግሊዝ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝታቸው ለጀርመን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርሚጉዌል በርገር እንዲሁም ለእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጄምስ ዱድሪጅ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የአንድ ወገን የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ለማድረግ ሲወስን በዋነኝነት የትግራይን ህዝብ ከተጨማሪ ሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግና የእርሻ ወቅት አልፎ በመጭዎቹ ዓመታት የምግብ እጥረት ቀውስ እንዳይገጥም ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ለህዝቡ ከ400,000 ኩንታል በላይ ምግብ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን እና ነዳጅ በመጋዘኖች ክምችት መቀመጡን ገልፀዋል።
በተጨማሪም በተመረጡ 6 የሰብዓዊ እርዳታ አጋሮች በኩል እንዲዳረስ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ እስከ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።
የአለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የህወሃትን አጥፊ አቋም ተረድቶ በግልጽ ማውገዝ እንደሚገባው በአጽንኦት ተናግረዋል።
እስከ አሁን ለተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍም አመስግነው ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪማቅረባቸውን ከሰላም ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version