Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አሸባሪው ትህነግን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ግንባር በመዝመት አሸባሪው ትህነግን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
የባሕር ዳር ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት ማኅበር የህልውና ዘመቻ አስመልክቶ ውይይት አድርጓል።
ውይይቱ ተመላሽ የሠራዊቱ አባላት ወደ ግንባር በመዝመት ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ያለመ ነው።
“አሸባሪው የትህነግ ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ክህደት መቼም ቢሆን አይረሳም” ነው ያሉት አባላቱ፡፡
በህይወት እስካሉ ድረስም የሀገራቸውን ህልውና እንደሚጠብቁ ነው የገለጹት፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ጊዜ ሳይሰጠው መጥፋት አለበት ያሉት የባሕር ዳር ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት ማኅበር ሰብሳቢ ወታደር አበበ ምስጋናው “ትናንት ለሀገራችን መከታ እንደሆንን ኹሉ ዛሬም ለጥሪዋ ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።
የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልምድ ሀገርን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
ምንጭ:-አሚኮ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version