አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሣምንት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለፀ፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን የገቢ ኮንትሮባንድ 47 ሚሊየን 535 ሺህ 362 ብር የወጪ እቃዎች ደግሞ 2 ሚሊየን 953 ሺህ 432 ብር በድምሩ የ50 ሚሊየን 488 ሺህ 794 ብር ግምት አላቸው ተብሏል፡፡
ከኮንትሮባንድ እቃዎቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመዋቢያ እዋቆች፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ መድሀኒትና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን 42 ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

