Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተለያዩ ሚኒስትሮች የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስትሮች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ባስተላለፉት መልዕክት÷ አባይ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት አስተሳሳሪ ገመድ፣ የሰላም ፣ አብሮ የመልማትና የማደግ አገናኝ ድልድይ ለመሆን ቃሉን አድሷል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ የአባይን ህልም ለመፍታት ለወጣችሁ ለወረዳችሁ የኢትዮጵያ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም መላው ኢትዮጵያውያን የአክብሮት ምስጋናችን እናቀርባለን ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version