አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፥ ‘‘ለ1442ተኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢድ አል አድሓ ዓረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፥ አብሮ አደረሰን’’ ብለዋል።
በዕምነቱ አስተምርሆ መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እንዲሁም እርስ በእርስ በመተሳሰብ እና በመተጋገዝ በዓሉ በደስታ እንድናሳልፍ እመኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚሁ አጋጣሚ እንደሃገር ከፊትለፊት ለሚጠብቁን የጋራ የቤት ስራዎች በአንድነት ስሜት በመተሳሰብ እና በመደጋገፍ ሃገራዊ ሃላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

