Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ የአስከሬን ሽኝት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ አስከሬን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ ሽኝት እየተደረገለት ነው፡፡
በሽኝት መርሃ ግብሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል፡፡
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በተወለዱ በ87 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡
ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በ1973 ዓ.ም በተደረገው 3ኛ ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማህበራት ምርጫ ከንቲባ በመሆን ተመርጠው ከ1973 እስከ 1981 ዓ.ም ድረስ በከንቲባነት አገልግለዋል

 

Exit mobile version