Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

1 ሺህ 442ኛው የአረፋ በዓል በጅግጅጋ ከተማ በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብሯል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 442 ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በአል በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ስቴድየም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡
በዓሉን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ፣ የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሐላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎችህዝበ ሙስሊም ጋር በመሆን የኢድ ፀሎትና ሰላት አብረው በመስገድ አክብረዋል ፡፡
 
ምክትል  ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ለመላው አለም የእስልምና ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብርም በመረዳዳት እንዲሁም የተቸገሩና የታመሙ ሰዎችን በመጎብኘት መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ ህዝበ ሙስሊም ምዕመናን በበኩላቸው በዓሉ ሰላም የሰፈነበትና እንደነበር በመግለጽ÷በዓሉ ትላንት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ማግስት መከበሩ ደስታቸውን እጥፍ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version