Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚላክ የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) “የመከላከያ ሰራዊታችን ውለታ ተከፍሎ አያልቅም” በሚል በአዲስ አበባ የየካ ክፍለ ከተማ ሴት አደረጃጀት አባላት ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚላክ የስንቅ ዝግጅት እያደረጉ ነው።
የክፍለ ከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ወሰኔ በየነ እንደገለፁት÷ የበሶ የገብስ እና የዳቦ ቆሎ የስንቅ ዝግጅት ነው እየተደረገ የሚገኘው፡፡
የስንቅ ዝግጅት ማስጀመሪያ መርሃ ግብርም የተካሄደ ሲሆን ÷ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ሴት አመራሮች እና የክፍለ ከተማው ሴት አደረጃጀት አባላት ተገኝተዋል ።

በስንቅ ዝግጅቱ ላይ ከ350 በላይ የሴት አደረጃጀቶቹ አባላት በጉልበትና በገንዘብ  ተሳትፈዋል፡፡

በዛሬው እለት እየተዘጋጀ የሚገኘው ስንቅ በማህበሩ ተወካዮች አማካኝነት በነገው እለት ለከተማ አስተዳደሩ የማስረከብ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
በትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version