አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ግዳጅ ቀጠና ያመራው የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር መሃመድ አህመድ የተመራው የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት አዲስ አበባ ስደርስ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታና በሌሎች አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ÷ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ በመምጣቱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ክልሉ ከሌሎች ሀገራት ጋር በሚዋሰንበት አካባቢ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሽብርተኝነት የተፈረጁትን እንደ አልቃይዳ እና አልሸባብን በመደምሰስ አኩሪ ድል እንደፈፀመ ይታወቃል።
ልዩ ሃይሉ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በአሸባሪው የህወሓት ጁንታ የተቃጣውን ሀገር የማፍረስ ተግባር ለመመከት ዝግጁነቱን ማሳየቱም የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

