Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ህወሀት ህጻናትን ለጦርነት መማገዱ የነገ ብሩህ ተስፋቸውን ከማጨለም ባለፈ ጨካኝነቱን በገሀድ ያሳየ ነው – የጌዴኦ ዞን የህፃናት ፓርላማ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሀት ህጻናትን አስገድዶ በጦርነት መማገዱ የነገ ብሩህ ተስፋቸውን ከማጨለም ባለፈ ለማንም የማይራራ ጨካኝ መሆኑን በገሀድ ያሳየ ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን የህጻናት ፓርላማ አባላት ገለፁ።
ድርጊቱን ዓለም አቀፍ ተቋማት በዝምታ ማለፋቸው ከሰብዓዊነት ይልቅ ለፖለቲካ አሻጥር ቅድሚያ መስጠታቸውን ያሳየ ነው ሲሉም የፓርላማ አባላቱ ገልፀዋል፡፡
በዞኑ የህጻናት ፓርላማ ዋና አፈ ጉባኤ ሙሉቀን ምትኩ አሸባሪው ህወሀት ህጻናትን የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ለጦርነት ሲያሰማራ የሚያሳዩ ምስሎች በመገናኛ ብዙሀን መውጣታቸውን እንዳሳዘነው ገልጾ፥ በሰብዓዊ መብትና በህጻናት ዙሪያ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን በይፋ አለማውገዛቸው የሚያሳፍር ነው ብሏል፡፡
ህጻናቱ በለጋ እድሜያቸው በጦርነት መሳተፋቸው የነገ ራዕያቸውን ከማጨለሙ ባለፈ ለስነ ልቦና፣ ለአካል ጉዳት እንዲሁም ለሞት የሚዳርጋቸው መሆኑ ተገልጿል።
የጌዴኦ ዞን ህጻናት ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ እንግዳ ካሳ በበኩሉ እኛ ትምህርታችንን እየተከታተልን የትግራይ ህጻናትና ታዳጊዎችን በጦር ሜዳ ማየት እግጅ የሚያሳዝን ነው ብሏል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ የህወሓት ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርን በማጋለጥ ለህጻናት ያለንን ወገኝተኝነት ልናሳይ ይገባል ተብሏል፡፡
የፓርላማው አባል ቸርነት ቦጋለ በበኩሉ ህወሓት ህጻናትን ለጦርነት ሲያሰማራ ዓለም አቀፍ ተቋማት በዝምታ ማለፋቸው የሚያሳፍር ነው ብሏል።
ፓርላማው በተለይ ተቋማቱ ድርጊቱን በዝምታ ማለፋቸው ከሰብዓዊነት ይልቅ ለፖለቲካ አሻጥር ቅድሚያ እንደሚሰጡ የሚያሳይ መሆኑን በመግለጽ ተቋማቱ ዝምታቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርቧል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version