አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እንደገለጹት ÷ምክር ቤቱ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡
ጉባኤው የክልሉ ምክር ቤት፣የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2013 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል፡፡
በተጨማሪም የክልሉን የ2014 በጀት ዓመት በጀት ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

